የኦሮሚያ ፖሊስ በ2018 የህጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ ማርሽ ባንድ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የማርሽ ባንድ መሳሪያዎች ለመግዛት በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Oromia Police Commission (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን)
በኦሮሚያ ፖሊስ የተዘጋጀ ግ/ጨ/02/2018 የበጀት ዓመት
የኦሮሚያ ፖሊስ በ2018 የህጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ ማርሽ ባንድ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የማርሽ ባንድ መሳሪያዎች ለመግዛት በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ኦሮሚያ ፖሊስ የሚገዛቸው ከዚህ በታች ቀርበዋል።
በዚሁ መሰረት የግዥው አይነት፡- የተለያዩ የማርሽ ባንድ መሳሪያዎች
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለውድድር ይጋብዛል።
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ስለመክፈላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን እና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% ሆኖ የሚያስዙት የጨረታ ዋስትና ከ500.000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንት ማቅረብ የሚችል። ይህውም ጨረታው በሎት የተከፋፈለ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ ለየብቻ በማዘጋጀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ለየብቻ አሽገው ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም በ2 /ሁለት/ ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል በመለየት በአጠቃላይ በ4 አራት ፖስታ ማለትም ቴክኒካል ኦርጅናል፤ ቴክኒካል ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ፋይናንሻል ኮፒ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቴክኒካል ኦርጅናል ውስጥ በማሸግ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን በራሱ ወጪ የማጓጓዣ መጫኛ እና ማውረጃ ወጪዎችን ሸፍነው በኦሮሚያ ፖሊስ ግምጃ ቤት ድረስ ማስረከብ ይጠበቅበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነድ ሲያዘጋጅ ቫትን ጨምሮ ማንኛውንም ወጪን ጨምሮ ማዘጋጀት አለበት፣ ይህ ካልሆነ ግን በተጫራቹ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ማንኛውንም ወጪ አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገበበት የመጨረሻ ቀነ ገደብ 13/02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 13/02/2018 ዓ.ም በግዥ መምሪያ ቢሮ ውስጥ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አ/አበባ ክ/ከተማ ቂርቆስ ላንቻ አካባቢ
ለተጨማሪ መረጃ እና ማብራሪያ፡- ስ.ቁ 0913108990 ወይም 0996054778 መደወል ይችላሉ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
