የዲላ ትምህርት ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Dilla Polytechnic College (የዲላ ትምህርት ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
የዲላ ትምህርት ኮሌጅ
ሀ. የተለያዩ እቃዎችን ማለትም
1 በ 6211 ፍራሽ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር: 10000.00
2 በ 6215 የማባዣ ቀለምና እስቴንስል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 6000.00
በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከላይ የተጠቀሱ እቃዎችን ዋጋ ቫትን አካቶ በመሙላት ኮሌጁ ለዚሁ ሥራ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ሰ/ በዚሁ መሰረት
1. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብርአጠናቀው የከፈሉ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቶች (VAT) ከፋይነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፤
3. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሣቸውን ማግለል አይችሉም፤
4. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፣
5. ተጫራቾች በጨረታው ለሚሳተፉባቸው ዕቃዎች ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ከላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፤
7. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
8. ኮሌጁ በጨረታ አሸናፊ ለሆነው ድርጅት ከፍያ የሚፈጽመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው፡፡
9. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቧቸውን ሠነዶች ዋናውንና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የዲላ ትምህርት ኮሌጅ የግልጽ ጨረታ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም በማለት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡ ጨረታው በ 16 ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት፣ በመሥሪያ ቤቱ የማኔጅመንት መሰብሰቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡
11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት በጨረታ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ማንኛውም ወጪ የጉምሩክቀረጥን ጨምሮ በመሸፈን ዕቃዎቹን የሚያስረከበው ዲላ ትም/ ኮሌጅ ነው።
12. ተጫራቾች ለጨረታ በሠነድ ላይ ያቀረቡት ዋጋ ላሸነፉባቸው ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እስከሚያስረከቡበት ጊዜ ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል ፡፡
13. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% በማስያዝ ከመሥሪያ ቤት የሽያጭ እና የግዥ ውል ይፈራረማሉ፡፡
14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ የዕቃዎቹን አይነት የአምራቹን ሥም፣ የተመረተበትን ሀገር የሞዴል ቁጥርና የተመረተበትን ዓመት ጭምር ማካተት ይኖርበታል። የእስፔስፊክሽን መግለጫ የሚያስፈልጋቸው እቃዎች በአይነት በፎቶና የአቅም መለያ እንደአማራጭ ይቅረብ፡፡
15. ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
16. የዕቃው ርከከብ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር የሚከናወነው የግዥው መሥሪያ ቤት ባለሙያዎች በሚያደርጉት የጥራትም ሆነ የዓይነት ምርመራ በ /Specification/መሠረት ትክከለኛነቱ ሲረጋገጥ ይሆናል፣
17. የጨረታ ሰነዱን ከዲላ ትምህርት ኮሌጅ ብር 100 በመከፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር በግዥ ማግኘት ይችላሉ፡
18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ እንዲሁም ብዛት የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ
ስ.ቁ 046-331-36-29
የዲላ ት/ኮ/ግ/ፋ/ን አስተዳደር ስልክ ቁጥር 046331-42-51
ፋክስ:-046-331-24-92
የዲላ ትምህርት ኮሌጅ
