Tender Detail

Tender Details

  • Company በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ
  • Address በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፣ኢትዮጲያ, Phone: 0913101514
  • Website
  • Deadline16 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-10-16 00:00:00
  • Categories Ict Equipment'S And Its Accessories , Furniture

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ ለኮሌጆች ለስልጠናና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ICTY Material (lot-1) እና Furniture Material (lot-2) አቅርቦቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ _ለመግዛት ይፈልጋል::

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ


የጨረታ ማስታወቂያ

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ ለኮሌጆች ለስልጠናና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ICTY Material (lot-1) እና Furniture Material (lot-2) አቅርቦቶችን  በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ _ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡-

  • ICTY Material (Lot-1)
  • Furniture Material (Lot-2)

እነዚህን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች መስፈርት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

1. በዘመኑ የታደስ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ::

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ::

4. የግዥ መጠን ብር 100,000 ( አንድ መቶ ሺህ ብር ) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ።

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1- 4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ( እስፔስፍኬሽን ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር ) በመክፈል ከቢሮ የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት (አፋር ሠመራ) ክፍል ማግኘት ይችላሉ ።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቴክኒከና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የተቋማት ፍትሀዊ ስርጭት ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በቢሮው ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0913101514/0938360959 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ ሠራ ሲመጡ ከተማ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ውስጥ እንገኛለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም፡፡

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ  

Save Tender