መ/ቤታችን በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን የዳዬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚተዳደሩ መንገድ ግንባታና ጥገና ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አይሱዙ ደብልጋቢና፣ ሚኒ ጋቢና፣ እና ሚኒባስ መኪናዎችን ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
ድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር-ሲ/መ/ባ/0/014/2018
መ/ቤታችን በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን የዳዬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚተዳደሩ መንገድ ግንባታና ጥገና ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አይሱዙ ደብልጋቢና፣ ሚኒ ጋቢና፣ እና ሚኒባስ መኪናዎችን ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የመኪናው አይነት |
ብዛት |
ጠቅላላ ተሽከርካሪ የስራ ቀን |
የስራ ቦታ |
|
1 |
ደብል ጋቢና |
4 |
1080 |
በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ዞን |
|
|
ሚኒ ጋቢና |
4 |
1080 |
|
|
2 |
አይሱዙ |
3 |
810 |
በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ዞን |
|
3 |
ደብል ጋቢና |
4 |
1080 |
በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን |
|
|
ሚኒ ጋቢና |
4 |
1080 |
|
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን፣ ከሚፈልገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የስሪትን ዘመናቸው ለሚኒ እና ደብል ጋቢና አ.አ.አ 2008 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም አይሱዙ እና ሚኒ ባስ አ.አ.አ 2010 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከባለስልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ። የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 0.5% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራነስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ተሽከርካሪዎችን ወደ ስራ ያላስገባና ውላቸው የተቋረጠ የተሽከርካሪ አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ ማወዳደር አይችልም፡፡
- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446
ሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን
ሐዋሳ
