በደ/ኢ/ክ/መ/ፋ ዞን ሣውላ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለመ/ቤቱ መስመር ጥገና እና ለሱቅ ሽያጭ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ቧንቧና መገጣጠሚያ ዕቃዎችንና ቆጣሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሳውላ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢ/ክ/መ/ፋ ዞን ሣውላ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለመ/ቤቱ መስመር ጥገና እና ለሱቅ ሽያጭ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ቧንቧና መገጣጠሚያ ዕቃዎችንና ቆጣሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፡- በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መረጃዎች አሟልታችሁ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የሚፈለጉ መረጃዎች፡-
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- በዘርፉ የተመዘገቡበት ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማረጋገጫ
- TIN No /የግብር ከፋይነት መለያ
- የVAT ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት
- የጨረታ ማስከበሪያ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ እና
- ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዶችን አሪጅናል ለየብቻ በአንድ ፖስታ ማሸግ ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 60 ቀናት ሲሆን ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የጨረታው አሸናፊው በጨረታው ያሸነፈውን ዕቃ ንብረት እስከ ድርጅቱ ድረስ በራሱ የትራንስፖርት ወጪውን ሸፍኖ የሚያቀርብ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚከናወንበት ቦታ በሣውላ ከተማ ውሃ አገ/ት ድርጅት ሲሆን ጨረታው ከታወጀበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912913677/0912796689/0924027461 ደውላችሁ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የሣውላ ከተማ ውሃ አገ/ት ድርጅት
