ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለቦንጋ፣ ቦይታ፣ መዓዝ እና ወዞ ዙሪያ ወልድሃኔ ከተማ ለሚገነባቸው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች የውሃ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
SOUTHWEST CONSTRUCTION CORPORATION (የደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለቦንጋ፣ ቦይታ፣ መዓዝ እና ወዞ ዙሪያ ወልድሃኔ ከተማ ለሚገነባቸው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች የውሃ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት
- የግዥ ፈፃሚ መ/ቤት - ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
- የግዥ ዘዴ - አገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ
- የግዥ መለያ ቁጥር -002/2018
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-
- የግብር ከፋይነት መለያ ሠርተፊኬት ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ እና በጨረታ ለመሣተፍ ከገቢዎች ፍቃድ ያላቸው፣
- ከተለያዩ ተቋማት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያላቸው ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜና ቦታ፡-
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት/ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /እምስት መቶ ብር/ በደቡብ ኮንስትራክሸን ኮርፖሬሽን የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000615509209 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልል ቦንጋ ከተማ 03 ቀበሌ አካባቢ ከሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ቢሮ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 6:30 እና ከቀኑ ከ7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በማግስቱ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- በጨረታው አከፋፈት ሂደት የሚገኙ ህጋዊ ወኪሎች የውክልና ማረጋገጫ መያዝ ይጠበቅባችኋል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አለመገኘት የጨረታውን እከፋፈት ሂደት እያስተጓጉልም።
- የጨረታ ዋስትና -
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ሁለት ከመቶ /2%/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ከ90 /ዘጠና ቀናት ወይም ሦስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና በባንኮ ዋና መ/ቤት የተረጋገጠ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- የጨረታ ሠነድ አቀራረብ ሁኔታ፡-
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት፣ የግብር ከፋይነት ሠርቲፊኬት እና የታክስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተደገፈ CPO ኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ፋይናንሻል ዶኩሜንት ዋና እና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳሉ፡፡ የኮፒና ኦርጅናል መለያየት ካለ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ካላስያዙ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፣
- ባቀረቡት የዋጋ ማቅረቢያ እና የመጫረቻ ሰነድ ላይ እራስዎ ስለመሙላትዎ የድርጅቱ ሙሉ አድራሻ አንዲሁም ፈርማ እና ማህተም ማረጋገጥ ይኖርበታል።
- በጨረታ ሰነድ ላይ ቅሬታ ካለ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ቀናት ውስጥ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሎም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0927549359 /0913913138
የደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ቦንጋ
