Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline15 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security50,000.00
  • opening date2025-10-15 00:00:00
  • Categories Chemicals And Reagents

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አጠቃላይ የፅዳት ኬሚካሎች እና ግሊሲሪን በቋሚነት ሊያቀርቡ የሚችሉ እምራች ድርጅቶችን ብቻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T576

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አጠቃላይ የፅዳት ኬሚካሎች እና ግሊሲሪን በቋሚነት ሊያቀርቡ የሚችሉ እምራች ድርጅቶችን ብቻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል። ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ለሥራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በዘርፉ (ፈሳሽ እና ወይም ደረቅ የነላ ሳሙና/ዱቄት ሳሙና/በረኪና/ ግሊሲሪን) በማምረት ሁለት (2) ዓመት እና ከዚያ በላይ የሠሩ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በዘርፉ ከኢትዮጵያ የጥራትና ደረጃዎች ማረጋገጫ ባለስልጣን የጥራት ማረጋገጫ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የተሰጠ የአምራችነት የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፣ የተፈላጊውን ምርት ናሙና ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00/ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንከ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T576 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ከፍል እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-4028/8025

ኢ-ሜይል: AynalemAy@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

Ethiopian የኢተዮጵያ

Save Tender