በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ _ ኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ማሰራት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ማታወቂያ ቁጥር 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ _ ኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ማሰራት ይፈልጋል።
የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
* ቪዲዮ ካሜራ
* ሞንታርቦ
*ማይክ ከነስታንዱ
በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
1. በዘርፉ የተሰማሩ እና የታደሴ ንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና በዚህ የተደራጁ እና ስለ ድርጅታቸው ሙሉ መረጃ የሚያሳይፕሮፋይል እንዲሁም በዘርፉ መልካም የስራ ልምድ በማያያዝ ሰነዱ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 150.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) በመከፈል ከመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 7ተኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ፣
3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጀ ከሆነ ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. በጨረታ ላይ ያወጣናቸው እቃዎች በሙሉ ኦርጅናል እና ጥራቱን የጠበቀ ሆነው ማቅረብ የሚችሉ ፣
5. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት መ/ቤት ድረስ ማምጣት አለባቸው፣
6. ተጫራቾች ለገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫት በመጨመርበሰም የታሸጉ ኤንቨሎፕ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 7ተኛ ፎቅ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
7. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ወይም _ በሚያቀርቡት እቃዎች ማቅረብ አለባቸው፣
8. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ውል የተገባባቸውን እቃዎች በአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝና ከቢሮው የግዥ አገልግሎት ዳይሬከቶሬት የውል ስምምነት መፈጻም ይኖርባቸዋል፣
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለıo ተከታታይየስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፣
10. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
11. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣
አድራሻ፡- ሃያ ሁለት መገናኛ ለም ሆቴል ኤልሳ ቆሎ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111 56 23 05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
