በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ ያገለገሉ የቤትና የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ የእጅ መሳሪያዎች (Hand Tools) እና ሌሎች ያገለገሉ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ቲ-01/2018
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ ያገለገሉ የቤትና የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ የእጅ መሳሪያዎች (Hand Tools) እና ሌሎች ያገለገሉ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የታደሠ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች አስፈላጊውን ማስረጃ በማያያዝ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የእቃዎችን ሁኔታ በዲስትሪክቱ ግቢ በአካል በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መመለከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ 2% ያላነሰ በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (CPO) ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 15 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጐ ከ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ በሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ በበዓል ወይም በእሁድ ምክንያት ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ወይም ሲፒኦ (CPO) ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ እንደተገለፀ አስፈላጊውን ውል በአካል ቀርቦ መፈረም አለበት፡፡ ይህን ባይፈፅም ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሳስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000322269165 (ERA D/M Dist 'B') ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ በመያዝ ደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ቢሮ ቁጥር 15 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይቻላል። ማንኛውም ተጫራች የሰጠው መወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታ ውጤት እስኪታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡ አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ገንዘብ ክፍያ በመፈፀም ንብረቱን ማንሳት ይኖርበታል፡፡
ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0587713052, 0911984416 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
ደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
