ድርጅታችን ለ2018 በጀት ዓመት ለሠራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ (የሥራ ልብስ) ማለትም ሸሚዝ ብዛት 192 ከረቫት ብዛት 126፤ ሙሉ ልብስ ብዛት 188፣ ሙሉ ቱታ ብዛት 450 እና ጋዋን ብዛት 604 በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/18
ድርጅታችን ለ2018 በጀት ዓመት ለሠራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ (የሥራ ልብስ) ማለትም ሸሚዝ ብዛት 192 ከረቫት ብዛት 126፤ ሙሉ ልብስ ብዛት 188፣ ሙሉ ቱታ ብዛት 450 እና ጋዋን ብዛት 604 በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ከሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማመለስ ብር 300.00 ከፍል በመግዛት ፋይናንሺያል የቴከኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 በባንክ ከፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው::
ጨረታው 18/2/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴከኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶከመንቶች የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገጽ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
