በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ከመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን ለመግዛትና ለማሰራት ስለሚፈለግ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መመዘኛዎችን የሚያሟሉና በዘርፍ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ ለመግዛት ይፈልጋል።
የአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 21/2018 ዓ.ም
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ከመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን ለመግዛትና ለማሰራት ስለሚፈለግ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መመዘኛዎችን የሚያሟሉና በዘርፍ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ ለመግዛት
ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች የኮምፒውተር ቀለሞች እና የአላቂነት ባህሪ ያላቸው እቃዎች
ሎት 2 የጽዳት እቃዎች
ሎት 3 የህትመት ስራዎች
ሎት 4 የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች
ሎት 5 ቋሚ እቃዎች ፈርኒቸር/
ሎት 6 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች ብትን ጨርቅ ጫማዎች
ሎት 8 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገናዎች
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው::
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው::
3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የግዢው መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡
5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100/ አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን/የስ/ሂደት ቢ.ቁ 03 በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰአት መውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ለግዥው አይነትም ሆነ መጠን በጨረታው ሙሉ ለሙሉ መሙላት አለባቸው ማለትም ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት በሙሉ የተዘረዘሩትን እቃዎች መሙላት አለባቸው።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መስሪያ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃዎችን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ
9. መ/ቤቱ የእቃዎችን ናሙና የሚፈልጉ ከሆነ ተጫራቾች የተጠየቁትን ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው ጨረታው የሚለየው በጥቅል ዋጋ ነው::
11. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
12. ተጫራቾ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የእቃ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ባንከና በአቢሲኒያ ባንከ ብቻ በሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ/በጽ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስያዝ አለባቸው፤
13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ዋና ኦርጅናል በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ስም ፊርማና ሙሉ አድራሻ በመፃፍ ለእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አሰ/ደ/ስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት እስከ 15ኛው ቀን እስከ 11፡30 ሰአት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ጨረታው በ16 ቀን 4፡30 ሰአት ተዘግቶ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በ5፡00 ሰአት በገልጽ ይከፈታል፡፡
14. በማንኛውም ሁኔታ ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ መጫረት አይችልም።
15. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡አሸናፊ የሆነ ድርጅት በግዥ ፈጻሚ መስሪያቤት አቅራቢያ በሚገኝ ዐ/ህግ ጽ/ቤት በመቅረብ 10% ውል በመግባት ለግዥ ፈጻሚ መስሪያቤት ንብረት ከፍል ማስረከብ አለባቸው፡፡
16. ጨረታ ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፣ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል፣
17. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሄራዊ በአላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
18. 18. የመስሪያቤቱ መገኛ ከዞኑ ደ/ብርሀን ከተማ 86 ኪሜትር ከአዲስ አበባ ደግሞ 130 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
19. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912841935 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአ/ብ/ክ መንግስት የእ/ወ/ፍ/ቤት/የግ/ን/አስ/ቡድን/መሪ የስራ ሂደት
