በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን እና ያገለገሉ ብረታ ብረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-02/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን እና ያገለገሉ ብረታ ብረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስስሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ -
1. ተጫራቾች በዘርፋ በዘመኑ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር / TIN No /ያላቸውና ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች ለመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ የሚሳተፉ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ እና ለመመዝገባቸው የምስከር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ ።
2. የመኪና ጥገናውን በአግባቡ በተጠየቀ ጥያቄ መሰረት ጥራቱን ሳያጓድል መስራት የሚችሉ።
3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን፤ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን ማስፈር አለባቸው::
4. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ 10,000 ብር የብረታብረት ሽያጭ 5,000 ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም አን/ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በመሂı ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦሪጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት፡፡ የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ እና የብረታ ብረት ሽያጭአይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በዚሁ እለት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።7.16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግስት የሥራ ቀን ይከፈታል።
8. የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ በተመለከተ በሰሜን ሸዋ ዞን ደ/ብርሃን ከተማ ጋራዥ ወይም ቅርንጫፍ የከፈተና መከፈት የሚችል መሆን አለበት።
9. ተጫራቶች የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ እና የብረታ ብረት ሽያጭ አይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይንም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፤ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት፤ ከሎት ማጉደል አይችሉም።
10. ከአንድ ጨረታ በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ በተናጠል በየሎቱ ለየብቻው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
11. የብረታ ብረት ሽያጩን በተመለከተ የብረታ ብረት አቅላጭነት ንግድ ፈቃድ ያለው ተጫራች መሆን አለበት።
12 በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦርጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል።
13. በማንኛውም የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ ለአገልግሎት ከብር 10,000/አስር ሺህ/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ 3% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል።
14. ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግና በፍሉድ መደለዝ አይፈቀድም:: ምንአልባት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ ስህተት ቢፈጠር አንድ ሰረዝ አድርጐ ስለመሰረዙ መፈረም አለበት።
15. የአንድ ሰነድ መሸጫ ዋጋ 100 ብር ነው።
16. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
17. ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተ ሰሜን 10 ኪ/ሜ ርቀት በደብረ ብርሃን መስመር ላይነው::
18. ለበለጠ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 011-632-01-47 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
