የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቆሬ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀከት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የDomestic Pump አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ DCE/SF/139/2025
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቆሬ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀከት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የDomestic Pump አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የስራ ዝርዝር |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን
|
|
|
Supply install, test & Commission
|
DCE/SF/139/2025
|
28/01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00
|
28/01/2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15
|
ስለሆነም ፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ እና አቅርቦት አስተዳደር መምርያ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መስከረም 28/2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
7. አንድ ተጫራች ለአንድ ዕቃ መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ሞዴል/ብራንድ/ ብቻ ነው ፤ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር፡- 0114-40-34-34/33 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72 WWW.dce-et.
com /Email: info@dce-et.com
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርኘራይዝ
