የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኝ በ UAE የተመረተ BOROUGE HDPF PE 100 እስክራፕ በብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Gosh Meda Pipe & Plastic Manufacturing Enterprise (የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት)
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ጨ/003/2018
የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኝ በ UAE የተመረተ BOROUGE HDPF PE 100 እስክራፕ በብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የእስክራፕ አይነትና መጠን ድርጅቱ ድረስ በአካል በመገኘትና በማየት በድርጅቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
|
ተ.ቁ |
የእስክራፕ አይነት ዝርዝር መግለጫ |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
BOROUGE HDPE PE 100 እስክራፕ |
ኪ.ግ |
74,000 |
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ድርጅቱ ወደሚገኝበት ደሴ/ ገራዶ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ ወይም በድርጅቱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000184463567 ወይም በድርጅቱ አባይ ባንክ አካውንት ቁጥር 2032111046627062 ላይ የጨረታ ሰነዱን መግዣ ዋጋ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የHDPE እስክራፕ እና ፓሌት ጣውላ ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ብር ማስያዝ አለባቸው፤ ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም፡።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የHDPE እስክራፕ የሞሉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ በጥሬ ብር ማስያዝ አለባቸው፤ ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 6 በመገኘት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 6 በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በይፋ ይከፈታል፤ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በብሔራዊ ደረጃ የሚከበሩ የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፤
- ድርጅቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ድርጅቱ ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት መጠኑን በማየት ዋጋ መሙላት ይችላሉ። የግብአቱ መጠን ከላይ በማስታወቂያው ላይ ከተጠቀሰው መጠን ሊበልጥም ሊያንስም ይችላል በመሆኑም አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች በአካል የተገኘውን ግብአት ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይኖርበታል። በተናጠል በመወዳደር ለግብአቱ ዋጋ ማቅረብ ይቻላል። በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ድርጅቱ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0991841910/0923751571/0920781579 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ደሴ ገራዶ አግሮስቶን ቅጥር ግቢ
የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት
