የቦሌ ደ/ም/ቅ/ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባዔ አስተዳደር በቤተ ክርስቲያንኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማሰራት ላይ ይገኛል::
የቦሌ ደ/ም/ቅ/ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባዔ አስተዳደር
በድጋሚ የወጣ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ!
የቦሌ ደ/ም/ቅ/ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባዔ አስተዳደር በቤተ ክርስቲያንኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማሰራት ላይ ይገኛል:: በአሁኑ ወቅት የግንባታው የመጀመሪያ ምዕራፍ የተጠናቀቀ በመሆኑ የሁለተኛውን ምዕራፍ (Phase II) ለማሰራት ይፈልጋል::
ስለሆነም ይህንኑ ሥራ ለማከናወን ፍላጎት፣ ችሎታና ልምድ እንዲሁም ለ2017 ዓ.ም የታደስ የንግድና ሥራ ፈቃድ ያላችሁ እና በተመሳሳይ ሥራ ያላችሁን ልምድ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ደረጃ አምስት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ የሥራ ተቋራጮች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት አሥር ቀናት ውስጥ በደብሩ የመጠለያ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው የልማት ኮሚቴ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ከፍሎ በመውሰድ በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ ዘወትር በሥራ ስዓት ለልማት ኮሚቴው ጽ/ቤት እንድታቀርቡ እንጋብዛለን::
ጨረታው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተወካዮች፣ የቦሌ እና ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተወካዮች፣ የደብሩ ሰበካ ጉባዔ፣ የልማት ኮሚቴ እና የአስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በጨረታው ማስገቢያ የመጨረሻ ዕለት ማግስት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሰበካ ጉባዔው አስተዳደር ጽ/ቤት ይከፈታል::
የሰበካ ጉባዔው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::
የደብሩ ሰበካ ጉባዔ አስተዳደር
