በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የካ ቦሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018 አ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮና የት/ት እስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የኤሊከትሮኒከስ እና ፣ የህትመት ስራዎች፣የላብራቶሪ እቃዎች ፤ የስፖርት ዕቃዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ እንዲሁም አጋዥ መጽሀፍቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የየካ ቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የካ ቦሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018 አ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮና የት/ት እስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የኤሊከትሮኒከስ እና ፣ የህትመት ስራዎች፣የላብራቶሪ እቃዎች ፤ የስፖርት ዕቃዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ እንዲሁም አጋዥ መጽሀፍቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
|
የሎት ቁ. |
የሎት ዝርዝር |
የሲፒኦ መጠን |
|
ሎት1 |
የደንብ ልብስ |
20000 |
|
ሎት.2 |
አላቂ የት/ት እና እስቴሽነሪ ዕቃዎች |
15000 |
|
ሎት3 |
የኤሊክትሮኒክስ መሳሪያ ዕቃዎች |
15000 |
|
ሎት4 |
የስራ እና የደንብ ልብስ ስፌት |
15000 |
|
ሎት5 |
አላቂ የጽዳት ዕቃዎች |
15000 |
|
ሎት6 |
ፈርኒቸር ቃሚ እቃዎች |
15000 |
|
ሎት7 |
አጋዥ መጽሀፍ |
15000 |
|
ሎት8 |
የላብራቶሪ እቃዎች |
15000 |
|
ሎት9 |
የእስፖርትና የሙዚቃ መሳሪያ እቃዎች |
15000 |
|
ሎት10 |
ጥገና ስራዎች |
15000 |
በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ-
1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት፡፡
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
3. የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት፡፡
4. ተጫራቹ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው መሆን አለበት፡፡
5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በየካ ቦሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ(CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፉበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
6. የጨረታ ጊዜ ጸንቶ የሚቆየው 60 ቀን ብቻ ነው፡፡
7. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ከት/ቤቱ የፋይናንስና ግዢ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 04 የጨረታ ሰነዱን /በየሎቱ/ ለ1 ሎት የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች ለሚያመርቱት ምርት ብቻ ከከፍያ ነጻ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማጻፍ እና ለማያመርቱት ምርት/ዕቃ/ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛት እና በየሎቱ ተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ ፡፡
8 አማራጭ የጨረታ ሀሳብ ተቀባይነት የለውም፡፡
9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቾች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ የመስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት እና ማስረከብ አለበት፡፡
10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
11. ተጫራቾች ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዶችን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ከማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በታሸገ ፖስታ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ በቢሮ ቁጥር 005 ይከፈታል፡፡ ነገርግን ከኛው ቀን በዓል የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታ እና ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
13. ዘግይተው ወይም በከኛው ቀን የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
14. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ እንደተገለጸለት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒዮ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ አለበቸው፡፡
15. ተጫራቹ ባሸነፈበት የዕቃዎች ብዛት ላይ መስሪያቤቱ 20% ወደ ላይ 20% ወደታች አድርጎ መግዛት ይችላል። እንዲሁም ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- በለሚ ኩ/ ክ / ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ስሙ ጨሪ አካባቢ ጌቱ አደባባይ ገባ ብሎ
የካ ቦሌ ቅድመ አንደኛና የመጀ/ደ/ት/ቤት ስልከ ቁጥር 0118932455
ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የካ ቦሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት
