በኢትዮጵያ ኤሌክትሪከ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን የከባድ፣ መካከለኛ እና ቀላል ተሽከርካሪዎችን ለ3 ዓመት በሚቆይ ውል ተጫራቾችን አወዳድሮ የጥገና አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል::
Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ኢኤአ-ባሪ/ግብጨ/006/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪከ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን የከባድ፣ መካከለኛ እና ቀላል ተሽከርካሪዎችን ለ3 ዓመት በሚቆይ ውል ተጫራቾችን አወዳድሮ የጥገና አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል::
በመሆኑም፡-
ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና ብቃት ያለው ጋራዥ ጥገና ለማድረግና ለማደስ መወዳደር ይችላል::
ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና ብቃት ያለው ድርጅት የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይቻላል:: በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ቢሮ ቁጥር 408 ስልክ ቁጥር 058-320-6999/6775 ባህር ዳር
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ::
ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የንግድ ስራ ፈቃድ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ/ VAT/ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸዉ::
ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO፣ በባንከ ጋራንት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ማስያዝ አለባቸዉ::
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እስከተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በተ.ቁ 3 በተገለጸው አድራሻ ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
ተጫራቾች ከመንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን የተሰጠ የስራ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል::
ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ማቅረብ አለባቸው::
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ባይገኙም በባሕር ዳር ሪጅን ሰፕላይ ቼይን፣ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 408 መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል::
ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባህር ዳር ሪጅን
