በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደጀን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በአልማ በጀት የትኖራ ቀበሌ የቅድመ መደበኛ /አፀደ ሕፃናት/ የመማሪያ ከፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
የግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር -1
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደጀን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በአልማ በጀት የትኖራ ቀበሌ የቅድመ መደበኛ /አፀደ ሕፃናት/ የመማሪያ ከፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደርየምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የተሰማራ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
3. በግንባታ ሥራ ደረጃ 7 GC/Bc እና ከዚያ በላይ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
4. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
5.ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የግዥው መጠን ከ200000/ ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት/ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
6.ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር1-5 የተዘረዘሩትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የግንባታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሥሪያ ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው ::
9. ተጫራቾች የተጠየቀውን የትምህርት ቤት ግንባታ ሥራ በጥራት መሥራትና ማስረከብ አለባቸው፡፡
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይውሎ በ31ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡30 ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት 3:30 ታሽጎ 4:00 /አራት ሰዓት/ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ይከፍታል።
11. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ዝግ /በአል/ የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል።
12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. የጨረታው ተሳታፊዎች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር04 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0587760443 መደወል ይቻላል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
