የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ፡- ሎት 1 የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ግብዓት ግዥ፤ ሎት 2. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
Addis Ababa City Environmental protection Authority (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/አካ/ጥ/ባ/ስ/ግ/ጨ/ቁ/01/2018 ዓ.ም
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ፡- ሎት 1 የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ግብዓት ግዥ፤ ሎት 2. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ፡-
ለሎት1 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/
ለሎት2 ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር /CPO/ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች ለሚገዙት ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ይከፍላሉ፡፡
- ህጋዊና የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና በግብር ሰብሳቢው መ/ቤቱ የዘመኑን የመንግስት ግብር የተከፈለበት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ከብር 50,000.00 /ሃምሣ ሺህ ብር/ በላይ ዋጋ ባለው ግዥ ላይ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች በተጨማሪ አሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፤ የጨረታ ሰነድ በሚያስገቡበት ጊዜ የድርጅቱ ማህተም ሰነዱ ላይ መደረጉን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የክፍያ ትዕዛዝ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች አሸናፊ ድርጅቶች ለሚያቀርቧቸው የውሉን ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ያስይዛሉ፡፡
- ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የዕቃ ዋጋ /አገልግሎት/ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀን ጨረታው ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ዋጋ ማቅረቢያ ሲሞሉ ፋይናሽያል ኦርጅናል እና ፋይናንሽያል ኮፒ በተጨማሪም ቴክኒካል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ኮፒ ብቻ ብቻውን በፖስታ ማሸግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ናሙና የሚያስፈልግ የዕቃ አይነት ከሆነ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው። ካልሆነ በተሰጠው እስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ቢፈልጉ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሚያስገባው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0118332513 ደውለው ያነጋግሩ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
