Tender Detail

Tender Details

  • Company በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
  • Address አዳማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 11 043 690
  • Website
  • Deadline08 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-08 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Spare Parts , Stationery Materials , Office Equipment

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥ ፍላጎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር A-01/2018

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥ ፍላጎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1) የቢሮ እና የስልጠና አላቂ የፅህፈት መሳሪያ

2) ልዩ ልዩ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች

3) የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችና የተሽከርካሪ አላቂ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ለመፈፀም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ የሆነ ነጋዴ /ተጫራች/ በጨረታው ሊወዳደር ይችላል፡፡

1. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይሰርተፍኬት ፣ የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት መታወቂያ ሰርተፍኬት እና ካለፉት 3ወር የቫት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች ያወዳድራል፡፡

2. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሰነዱ ላይ በተገለፀው የገንዘብ መጠን መሰረት በኢትዮጵያ ባንከ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርበታል።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልጽ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በመፃፍ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቪሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ 300.00 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ አዳማ ሳይንስና ቴከኖሎጂ ዩንቨርሲቲ በር 200 ሜትር ዝቅ ብሎ ከሚገኘው የሜ/ድ ዕዝ ጠ/መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይቻላል።

➢ አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% በኢ/ያ ባንክ የተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

➢ ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ እና በማራገፍ አዳማ የሜ/ድ ዕዙ ጠ/መምርያ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

➢ መስሪያቤቱ የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

➢ ጨረታው መስከረም 28/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሜ/ድ ዕዙ ግዥ ቡድን በሚያዘጋጀው ቦታ ይከፈታል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911043690 ወይም 0911025079 ይደውሉ፡፡

የሜካናይዝድ ዕዝ ግዥ ቡድን

Save Tender