ሠላም 16 የጋራ የመኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ስ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 በርታ ሪል ስቴት 6.4 ሄክታር ሳይት 1B+G+9 የጋራ ህንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ሠላም 16 የጋራ የመኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ስ/ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ግልጽ ጨረታ ቁጥር 01/2017
ሠላም 16 የጋራ የመኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ስ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 በርታ ሪል ስቴት 6.4 ሄክታር ሳይት 1B+G+9 የጋራ ህንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ኮንትራክተሮች፡
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value Added Tax) ተመዝጋቢ የሆኑ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (ሰርተፊኬት) ያላቸው
- በማንኛውም መስሪያ ቤቶች ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ እና በመንግስት የኮንስትራክሽን ስራ የግልጽ ጨረታ አፈጻጸም መመሪያ መስፈርት መሰረት ለመወዳደር ብቁ የሆኑ
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት BC-2/GC-3 እና ከዚያ በላይ የሆኑና አምስት ዓመት ተከታታይ የሰሩትን የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ። በየትኛውም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ህጋዊ ውል ገብተው ያለስራ ጥራት ጉድለት ያጠናቀቁ፣
- 2013 ዓ/ም ጀምረው ባለው ጊዜ ውስጥ በተመሳሳይ ስራ አሸንፈው ያጠናቀቁትን ፕሮጀክቶች በዝርዝር ከነመልካም አፈጻጸም ሰርተፊኬታቸው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የስራ ተቋራጮች ለወድድር ያቀረቡትን /ቴክኒካል/ ብቃት መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና /ኦረጂናል/ ኮፒ ሲጠየቁ አቅርቦ ማመሳከር አለባቸው። ይህ ተጣርቶ ኮፒ ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲሞሉ ከተ.እ.ታ. በፊት ያለ የነጠላ ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል።
- ቴክኒካል ውድድሩን ያላለፈ ተጫራች ፋይናንሻል ሰነድ አይከፈትም።
- የጨረታ ማስከበሪያ unconditional Bank Guarantee ወይም የክፍያ ማዘዣ CPO 500,000.00 በሠላም 16 የጋራ የመኖሪያ ቤት ኃ/የተ/ህ/ስ/ማህበር ለ 90 ቀናት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ቢድ ቦንድ ፋይናንሽያል ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻው፣ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በሁሉም ዶክሜንት ላይ ህጋዊ የሆነ የድርጀቱ ባለቤት ፊርማና ማህተም ያለበት ሰነድ መግባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ጨታውን ካሸነፉ እና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ካሟሉ በኋላ የግንባታ መሣሪያዎቻቸውን በቦታው አጓጉዘው ማድረስ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ማጭበርበር፤ ሙስና እና ማታለልን በተመለከተ ላለመፈጸም በኢትዮጰያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር እና የሚያስከብር መሆን አለባቸው።
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ።
- አሸናፊ የሚሆነ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት በኋላ ለውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፉት ዋጋ 10% Conditional Bank Guarantee ወይም (CPO) አሰርተው ውል መዋዋል ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ በጨረታ ሰነዱ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማድረግ፣ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል፣ ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ማስረጃ (ዋጋ) ላይ ስርዝ ድልዝ (ፍሉድን ጨመሮ) ካለበት ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
- ለጨረታ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት የማይቀየር (የጸና) ይሆናል።
ጨረታ የሚከፈትበትና የሚዘጋበት ቀን
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ የማይመለስ 500.00 ብር በማህበሩ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000554783531 በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በ selam16housingco@gmail.com አድራሻ በመላክ ለዚሁ ጨረታ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው ጥቅምት 3/2017 ዓ/ም 8 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳር ቤት አደባባይ እልልታ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ይከፈታል።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡
ስልክ +251972200000/+251918054115/+251913650252
አዲስ አበባ
