Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቦሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 0913172343
  • Website
  • Deadline29 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening date2025-09-29 00:00:00
  • Categories Office Equipment

በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቦሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቢሮ መጠቀሚያ እቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቦሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018

በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቦሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቢሮ መጠቀሚያ እቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደርየምትፈልጉ በመስኩ ለተሰማራችሁ ግለሰቦች (ድርጅቶች) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

1. የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ህትመት፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች (የፅዳት እቃዎች)፣ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ የማሽነሪ (ኮምፒውተርና መሰል እቃዎች) ጥገና፣ የተለያዩ ፈርኒቸሮች ጥገና ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ፣

2. ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ የደንብ ልብሶች 5000፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች 5000፣ ህትመት 5000፣ የዕዳት እቃዎች 5000፣ የማሽነሪ (ኮምፒውተርና መሰል እቃዎች) ጥገና 5000፣ የተለያዩ ፈርኒቸሮች ጥገና 5000፣ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋርማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በጽ/ቤታችን ፋይናንስና አስ/ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 6ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይናንስና አስ/ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ጨረታው በ6ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደርያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴከኒካል ዶከመንቶችን (የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ ኦርጅናልና እና የተጠየቁ አስፈላጊ የንግድ ፍቃዶችና መረጃዎች በተለያየ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለው ማለት አይችልም፡፡

 

9. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል፡፡

10. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል፡፡ አድራሻ፡- መገናኛ ቦሌ ከፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ፅ/ቤት ምድር (Ground) መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ. 0913172343 እና 0913541013 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደርቢሮ

የቦሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Save Tender