Tender Detail

Tender Details


በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም ባለው በጀት የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች፣ የፅህፈት ዕቃዎች እና የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፡- መ/ስ/ኮ/ግ/ጨ/002/18

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም ባለው በጀት የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች፣ የፅህፈት ዕቃዎች እና የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ መዝገባቸውን እና የግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ጨረታው የሚከናወነው በብሄራዊ የግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓትና ይህንኑ አስመልከቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው፡፡

3. ፍላጐት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ የሚችሉት እና የጨረታ ሰነዱ የሚመረመርበት በመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ አዋሽ ሰባት ኪሎ ነው፡፡

4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ ብቻ በመከፈል የተሟሉና በአማርኛ የተዘጋጁ ሰነዶችን መለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ አዋሽ ሰባት ኪሎ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚላከው በተጫራቾች ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው ሲሆን ሰነዱ ቢጠፋ ወይም ቢዘገይ ኃላፊነቱን የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

5. ሰነዱ የሚሸጥበት እና ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ፡- መለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ አዋሽ ሰባት ኪሎ ወደ ሰመራና ሀረር መገንጠያ ከባድ ጭነት ሚዛን ፊት ለፊት ግዥ ዴስክ ቢሮ እስከ 30/01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክበሲፒአ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ አዋሽ ሰባት ኪሎ በ30/01/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ30/01/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

7. ንብረቱን ገቢ የሚያደርጉት በመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ ንብረት ግ/ቤት አዋሽ ሰባት ኪሎ ነው፤ ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ በ033-5-40-06-19 ወይም 09-22-83-96-24 ይደውሉ፡፡ መለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ

Save Tender