Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሆኑ የግንባታ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያቁጥር፡-GGWW/0001/2018

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሆኑ የግንባታ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ለግዢ የቀረቡ እቃዎችና የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ሎት አንድ፡- የግንባታ እቃዎች፣ (ጨረታ ማስከበሪያ 10,000 ብር፡-

የጨረታው መስፈርት፡-

  1. የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፣ የቫት እና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኦላይን /online/ ሲስተም የተመዘገበ መሆን አለበት።
  3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት የጨረታ ሰነዱ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውከልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፣ ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና፣ ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በማሸግ ከላይ የተጠቀሱት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ / በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስተኛው/ ተከታታይ ቀናት ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት።
  7. የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀነ 8፡00 ሰዓት ይታሸግና በዚያው ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ደግሞ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

  1. በግዢ ኤጀንሲ በዕቃ አቅርቦት ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
  2. ተጫራቾች ያሸነፏቸው እቃዎች የጥራት ችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥራት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ተመላሽ መሆኑን።
  3. የቫት 7.5 ለወረዳው ገቢ የሚቆርጥ፣
  4. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፏቸው ማንኛውም እቃዎች የወረዳው ማዕከል ማለትም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሀል አምባ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የወረዳው ማዕከል ርቀት ከአዲስ አበባ 116ኪሜ ነው።
  5. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።

 

ለበለጠ መረጃ 011-3-36-06-31/011-3-36-01-46

 

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender