ድርጅታችን ስኬት ኢንተርናሽናል አክሲዮን ማህበር ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የከርሰ ምድርውሃ ቁፋሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስኬት ኢንተርናሽናል አክሲዮን ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ስኬት ኢንተርናሽናል አክሲዮን ማህበር ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የከርሰ ምድርውሃ ቁፋሮ ማሰራት ይፈልጋል።
- ተጫራች የከርስ ምድር ውሃ ቁፋሮ ለመስራት የሚያስችል የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬት ያለው፣
- ተጫራች ከዚህ ቀደም በተለያዩ ድርጅቶች /ተቋማት በሙያው ለመስራቱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው
- የጨረታ ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ክፍል 7ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 701 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100.000,00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ (Cpo) ማሲያዝ አለባቸው።
- ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ የሚሰሩበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ በድርጅቱ 7ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 701 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው መስከረም 30/2018 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ በ9፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጥቅምት 04/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ውል መፈራረም እና ሥራ መጀመር አለበት፣
- አድራሻ፡- መርካቶ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ነው
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 011.2.73.49.04 ይደውሉ
ድርጅቱ
