Tender Detail

Tender Details


በአራዳ ክ/ከ/ወ/2 የስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ በ2018 የበጀት ዓመት በሎት ከፋፍሎ ለማጫረታ ይፈልጋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ስ/ከ/ጤ/ጧ/01/2018

በአራዳ ክ/ከ/ወ/2 የስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ በ2018 የበጀት ዓመት በሎት ከፋፍሎ ለማጫረታ ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የተለያዩ ቋሚ እቃዎች፣ መድሃኒቶችና የላብራቶሪ ሬኤጀንቶች፣ ሎት2 የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ጨርቆችና ጫማዎች፣ ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ህትመቶች፣ ሎት3 የተለያዩ ጥገናዎች፣ የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት የሚሰጡ፣ የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከሪካሪዎች፤ የጀነሬተር ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ፤ የአይቲ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ፣ የለስላሳ አቅርቦትና መስተንግዶ የሚሰጡ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-

1. ከሚገዛው ዕቃ /አገልግሎት/ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No ማቅረብ የሚችሉ፣

2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምዝገባ የምስከር ወረቀት/በዌብሳይት የተመዘገቡ ተጫራቾች ከዌብሳይቱ ላይ ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች በተወዳደሩበት ሎት ላይ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ 2% ሲ.ፒ.አ (CPO) I በባንክ በተረጋገጠ በጤና ጣቢያው ስም ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡

5.ተቋማችን የሚገዛቸውን የአገልግሎት/ የዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 150 በመክፈል በአራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት አርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፓስታ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀውየጨረታ ሳጥን ውስጥ በአራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ግዥ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ያላካተተ፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጐ የማያቀርብ፣ ስርዝ ድልዝ ያደረገ እና አማራጭ ጨረታ የተጠቀሙ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

 

8. የጨረታው ሣጥን በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ3፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ አዳራሽ ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡

9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ጥራት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት በአራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ግዥ ቢሮ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ/ተጫራች ከውድድርውጭ ይሆናል፡፡

10. በቋሚ እቃዎች ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሰነዳቸው ጋር የፎቶና እስፔስፊኬሽን ማቅረብ አለባቸው ፎቶ አስፔስፊኬሽን ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድር ውጭይሆናል፡፡

11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያው እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

12. መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ 20% /ሀያ ከመቶ/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል።

13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፦ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አለፍ ብሎ ታደሰ ቸኮል ኮሜርሻል 100 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ስልክ +251 11 126 53 33/ 09 11 44 12 57 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

በአራዳ ክፍስ ከተማ ወረዳ 2 የስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ

Save Tender