የሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ከሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኢቢሲ ሬኤጀንት እና የተለያዩ የኬሚስትሪ ሬኤጀንት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአንድ አመት አቅራቢ መግዛት ይፈልጋል።
የሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ከሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ የኢቢሲ ሬኤጀንት
- የተለያዩ የኬሚስትሪ ሬኤጀንት
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአንድ አመት አቅራቢ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው
- የተማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 በመክፈል በሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 96 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን ዋና እና ቅጅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 96 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ማስገዛት ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል (ባይገኙም ይከፈታል) የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይፈጸማል።
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ጠቅላላ ድምር ስለሚሆን ሁሉንም መሙላት ይኖርበታል።
- ሆስፒታሉ እንደበጀቱ ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሬኤጀንት ብዛት መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
- አሸናፊው ድርጅት የሚቀርቡትን ሬኤጀንት ጥራታቸውን ጠብቆ በሀይቁ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አቅርቦ እንዳጠናቀቀ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል።
- የሚገዙት ሬኤጀንት ጥራታቸውን የጠበቀ መሆን አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር /0913808243 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
በአ/ክ/መ/በደ/ወሎ/ዞ/የሀይቅ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን
