Tender Detail

Tender Details

  • Company Wachemo University (የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ)
  • Address ሆሳዕና : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 465551910
  • Websitehttps://wcu.edu.et/
  • Deadline01 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
  • opening date2025-10-01 00:00:00
  • Categories Maintenance And Repair

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የቢሮ ማሽኖችን ማለትም የፎቶ ኮፒዎችና የፕሪንተሮች መለዋወጫዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል።

Wachemo University (የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ)


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የቢሮ ማሽኖችን ማለትም የፎቶ ኮፒዎችና የፕሪንተሮች መለዋወጫዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  • በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ አግባብነት ያለው ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት
  • በገቢዎች መ/ቤት የግብር ግዴታ መወጣታቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ።

 

የሎት ቁጥር

የግዥው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሰነዱ መሸጫ ብር

ጨረታ የሚቆይበት ቀን፤ ወርና ዓ.ም ሰዓት

የሚታሸግበት

የሚከፈትበት

1

ለቢሮ ማሽኖች ፎቶ ኮፒዎችና ፕሪንተር መለዋወጫዎች ግዥ

50,000

200

21/01/2018 ሰዓት 8፡00

21/01/2018 ሰዓት 8፡30

 

  1. ተጫራቾች በሌላ ተቋም በተመሳሳይ ሙያ ዘርፍ የሰሩበትን የስራ ልምድ ማቅረብ መቻል ይኖርባቸዋል። እንዲውም ከላይ የተጠቀሱትን የጥገና ዕቃዎች እስከ ዩኒቨርሲቲ በማቅረብ በአግባቡ መጠገን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000021178342 ገቢ በማድረግ ወይም በካሽ /በጥሬ ገንዘብ/ መክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመለዋወጫና አገልግሎት የእንዳንዱን ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የእቃውን ዝርዝር ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው በተሰጠው ስፔሲፊኬሽን ላይ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማሳረፍ 1 (አንድ) ኦርጅናልና 2 (ሁለት) ኮፒ በማድረግ ግዥና ውል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 21/01/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. የጨረታው ውጤትም ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ በስልክ እና በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
  6. አሸናፊ ድርጅት ዕቃዎቹን በራሳቸው ወጪ በማቅረብ የመጠገን ግዴታ አለባቸው፡፡
  7. አሸናፊ ድርጅት የሚለየው በአጠቃላይ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ይሆናል።
  8. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (ውል ማስከበሪያ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ማንኛውም ተጫራች በውል ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር አለበት።
  10. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 046-855-90-3/04685559163 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።

 

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

ሆሳዕና

 

Save Tender