የአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ኅ/የተወሰነ የገበያ ማእከል G+4 የእጅ ሞያ ብቻ በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ ዉስጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል።
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ኅ/የተወሰነ የገበያ ማእከል G+4 የእጅ ሞያ ብቻ በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ ዉስጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
ስለሆነም በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡
- በግንባታ ስራ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የግብር ክፍያ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
- የዘመኑን 2017 ግብር የከፈለ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የቴክኒክ እና የፋይናንስ ኦርጂናል እና ኮፒውን በግልፅ ለይተው ማቅረብ አለባቸው።
- የግንባታ ፍቃድ BC ወይም GC ኛ እና 5ኛ ደረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።
- ተጫራቾች ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺብር / በCBE እና በCBO ባንክ የጨረታ ማስከበርያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተመሰከረ ቼክ /CPO/ ወይም የባንክ ዋስትና በአርባጉጉ የገ/ህ/ሥራ ዩኒዬን ስም ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛዉም ተጫራች የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መዉሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ግንባታው የሚሰራበት ቦታ በአካል ከጎበኙ ቡኋላ መጎብኘታቸውን የሚያሳይ ደብዳቤ ከመስሪያ ቤታችን መውሰድ አለባቸው
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ ከ2:30-11:00 በዋና ቢሮአችን በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በመርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ 01 ቀበሌ ከአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ሰነዱን መግዛት ይችላል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 16ኛው ቀን 4፡00 አራት ሰዓት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የማወዳደሪ ሰነዳቸውን አስገብተው ይታሸግና በዚሁ እለት 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ሆኖም የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
- ማሳሰቢያ፡- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር /321 095 880/0912 934 586/0920 063 65 ደዉሎ መረዳት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን ።
በአርሲ ዞን የአርባጉጉ የገ/ህ/ስራ ዩኒዬን ኃ/የተወሰነ
