Tender Detail

Tender Details

  • Company Gamo Development Association (የጋሞ ልማት ማህበር)
  • Address አርባ ምንጭ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +2510468810434
  • Websitehttps://www.gammoda.org/
  • Deadline02 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-02 00:00:00
  • Categories Maintenance And Repair , Spare Parts

የጋሞ ልማት ማህበር/ጋልማ/ ዋና ጽ/ቤት በጋልማ የአርባ ምንጭ እርሻ ልማት ፣ በጋልማ የጋሮ ተሸከርካሪዎች ተገናና መለዋወጫ እና በጋልማ የአርባ ምንጭ እዞ ራንች ቅጥር ግቢ የሚገኙና ያገለገሉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች ፣ መለዋወጫዎች እና ሌሎች ያገለገሉ ንብረቶች ለቢሮና ለመኖሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Gamo Development Association (የጋሞ ልማት ማህበር)


ያገለገሉ ንብረቶች ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ እስካኒያ መኪናዎች፣ ኖቬዶች፤ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች እና ሌሎች ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጋሞ ልማት ማህበር/ጋልማ/ ዋና ጽ/ቤት በጋልማ የአርባ ምንጭ እርሻ ልማት ፣ በጋልማ የጋሮ ተሸከርካሪዎች ጥገናና መለዋወጫ እና በጋልማ የአርባ ምንጭ እዞ ራንች ቅጥር ግቢ የሚገኙና ያገለገሉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች ፣ መለዋወጫዎች እና ሌሎች ያገለገሉ ንብረቶች ለቢሮና ለመኖሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ-

1. ተጫራቶች እንደየንብረቶቹ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የማቅረብ/ በጥሬ ገንዘብ የማስያዝ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን በጨረታው ካሸነፉ ከሚገዙት ንብረት ላይ ታሳቢ የሚሆን ሲሆን በጨረታው ካላሸነፉ ያስያዙት ገንዘብ /ሲፒኦ/ ይመለስላቸዋል፡፡ የሚያስይዙት /CPO/ /ጥሬ ገንዘብ /በሠነድ ላይ በእታዎች ፊት ለፊት የተግለፀው ይሆናል፡፡

2. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ንብረቶች በጋልማ የአርባ ምንጭ እርሻ ልማት እና በጋልማ የጋሮ ተሸከርካሪዎች ጥግናና መለዋወጫ እና በጋልማ የአርባ ምንጭ አዞ ራንች ቅጥር ግቢ በማንኛውም የሥራ ሰዓት መመልከት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ማንሳት አለባቸው ካላነሱ ድርጅቱ ንብረቶቹ የቆዩበት 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በየቀኑ ኪራይ ያስከፍላል፣

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከተር ሥራ ከፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይጨምራሉ፣

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በጋሞ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ!

6. ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቹ/ ወኪሉ በቦታው ባይገኝም የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም፡፡

7. ልማት ማህበሩ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ከዚህ ጨረታ ጋር ተያያዥ ለሆኑ ጥያቄዎች በስልክ ቁጥር 0916482815 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

9. የድርጅቱ አድራሻ ፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግሥት በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ነው፡፡

የጋሞ ልማት ማህበር/ጋልማ/አርባ ምንጭ

Save Tender