Tender Detail

Tender Details

  • Company ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ
  • Address በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-6-81-63-85
  • Website
  • Deadline30 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price250.00
  • Bid Securityከጠቅላላ ዋጋ 2%
  • opening date2025-09-30 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Chemicals And Reagents , Flora And Horticulture

ወደራ ሁለገብ ገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ የአገልግሎት ጊዜያቸው የተቃረበ ኬሚካሎችንና የአትክልት ዘር በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ


 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግብርና ኬሚካልና የአትክልት ዘር ሽያጭ ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ወደራ ሁለገብ ገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ የአገልግሎት ጊዜያቸው የተቃረበ ኬሚካሎችንና የአትክልት ዘር በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

  1. በዚህ ንግድ ዘርፍ /ዘርፎች/ የህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ያላቸው፤
  2. የበጀት ዓመቱን ግብር የከፈሉ እና ከግብር ነጻ /Tax clearance/ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት /TIN/ እና የቫት ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መግዣ የማይመለስ ብር 250.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በዩኒየኑ አካውንት ቁጥር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠባሴ ቅርንጫፍ ሂሳብ ቁጥር 1000602970713 ወይም አባይ ባንክ 2049410105010815 በማስገባት እና ያስገቡበትን የባንክ ደረሰኝ በመያዝ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ/ ቢሮ ቁጥር 1 ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በሁለት የባንክ ፈራሚ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በዩኒየኑ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ ዋስትና አሲዘው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ቴክኒከ እና ፋይናንስ ዶክመንት በተናጠል ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ ፖስታዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት ኣካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ/በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት/ ቅዳሜ እስከ 6፡30 ሰዓት ጨምሮ /ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስር (10) የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ስለሆነ ማስገባት ይቻላል፡፡ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ይታሸጋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ/ በአስረኛው (10ኛው) ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ/ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 011-6-81-63-85/ 011-6-81-41-15 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

 

ወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተ

 

Save Tender