Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሀቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የፅህፈት መሳሪያ፣ የመኪና እቃ፣ የእንስሳት የፈውስ መድሀኒትና መገልገያ እና በአልማ በጀት የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር (ኮንባይንዲግ ዴስክ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የመርሀቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሀቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የፅህፈት መሳሪያ፣ የመኪና እቃ፣ የእንስሳት የፈውስ መድሀኒትና መገልገያ እና በአልማ በጀት የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር (ኮንባይንዲግ ዴስክ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን።

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር ኮፒውን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ የሚችል።
  2. የሞሉት ዋጋ ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፣ ከፈውስ መድሀኒቶችና መገልገያዎች በስተቀር፡፡
  3. እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ለፅህፈት መሳሪያና የተማሪዎች መቀመጫ እያንዳንዱን በብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) እንዲሁም የመኪና እቃ እና የፈውስ መድሀኒት እያንዳንዱን በብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ባሉት የካላንደር ቀናት ውስጥ ከቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቁርጥ ለፅህፈት መሳሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ለመኪና እቃ እና ለፈውስ መድሀኒት ለእያንዳንዳቸው 10,000 (አስር ሺህ ብር) እንዲሁም ለተማሪዎች መቀመጫ ወንበር ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሰፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ የውስጥ ግቢ ደረሰኝ ማሰያዝ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ዋናውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የመ/ቤቱን ስምና አድራሻ በመግለፅ በመ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በ3፡01 ሰዓት ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም
  9. በስልክ ቁጥር 011-1-32-01-36/005 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም ህዝባዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

 

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የመርሀቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender