Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline01 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-01 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የህትመት ውጤቶች መሸጫ ኪዮስኮች ግንባታ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 002/2018

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የህትመት ውጤቶች መሸጫ ኪዮስኮች ግንባታ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  • በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
  • የንግድ ምዝገባ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
  • የቫት ሰርተፍኬት
  • በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ

ከላይ በዝርዝር በቀረበው መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚሹ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤ የጨረታ ሰነዱን በነጻ እንዲወስዱ ያስችላቸዋል፡፡

የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ፣ ቢድ ቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒክ ዋና ሰነድ ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነባሩ ህንጻ ምድር ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም፡፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

* ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

 

Save Tender