Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


 

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 13/2018

 

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ መስከረም 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡

በመሆኑም

  1. በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
  3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ መስከረም 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. በዕቃ ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንከ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

 

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ

ቅ/ጽ/ቤት

የእቃ ግልፅ

እስከ 13/01/2018

14/01/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ -ኢ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  2. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ግቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  5. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ፡- 011-470 - 85-03

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

 

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender