የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተባባሪ ጽ/ቤት የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በአረንጓዴ ልማት ሊሰራ ከያዛቸው ተግባራት አንዱ ከሀይዎንዳይ ወደ ኡራኤል የሚወስደው የመንገድ አካፋይ ስራ በስታንዳርዱ መሰረት ለማልማት ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይን ግንባታ ስራዎች ፑል አስተባባሪ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር፡- 002/2018
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተባባሪ ጽ/ቤት የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በአረንጓዴ ልማት ሊሰራ ከያዛቸው ተግባራት አንዱ ከሀይዎንዳይ ወደ ኡራኤል የሚወስደው የመንገድ አካፋይ ስራ በስታንዳርዱ መሰረት ለማልማት ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። በዚህም መሰረት፡-
-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ ፈቃድ ያላቸው ተቋራጮች፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለሎቱ የተጠቀሰውን ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረት የባንክ ዋስትና /Unconditional Bank Guarantee/ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያውን ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት አንስቶ ቅዳሜን ጨምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ ሰነዶችን ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማደራጀት ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በ14 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ህንጻ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን በሚገኝበት 5ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አራተኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ አየር ላይ ውሎ በማግስቱ በ15ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገጾች ላይ ማህተምና ፊርማ አለማድረጋቸው የዋጋ ዝርዝር /Rate/ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ የዋጋ /Rate/ ያልተሞላበት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝር ዋጋ /Rate/ ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ስራዎች ግዥ ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ /ቢድ ቦንድ/ 300,000.00 ወይም CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረት የባንክ ዋስትና /Unconditional Bank Guarantee/ ለ90 ቀን የሚቆይ ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተባባሪ ጽ/ቤት ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ፡-
አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ሀይሌ ጋርመንት አደባባይ ፊት ለፊት የአስተዳደሩ ህንጻ በሚገኝበት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን
ስልክ ቁጥር፡-011-8-83-80-20
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዲዛይን ግንባታ ስራዎች ፑል አስተባባሪ ጽ/ቤት
