የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለስራ ክፍሎች የሚያገለግሉ መድኃኒቶችን እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለስራ ክፍሎች የሚያገለግሉ
ሎት 1 መድኃኒቶችን
ሎት 2 የላብራቶሪ ሪኤጀንቶችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለዕቃዎች የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) እና የታደሰ የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 15,000 በባንክ በተመሰከረ C.P.O /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በተለያዩ ፖስታዎች ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30- 11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463299263 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
