በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ በወረዳ 6 ክልል ውስጥ የሚገኘው የእውቀት አምባ ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ/ ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም. ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በወረዳ 06 ት/ፅ/ቤት የዕውቀት አምባ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ በወረዳ 6 ክልል ውስጥ የሚገኘው የእውቀት አምባ ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ/ ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም. ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 የደንብ ልብስ………………………………ብር 20,991.34
ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች………………………ብር 20,000.00
ሎት 3 የህትመት……………………………………ብር 2,180.98
ሎት 4 የህክምና እቃዎች…………………………...ብር 136.00
ሎት 5 የትምህርት መርጃ እቃዎች…………………ብር 8030.60
ሎት 6 የፅዳት እቃዎች………………………………. ብር 20,000.00
ሎት 7 የተለያዩ መፅሀፎዎች……………………….. ብር 630.00
ሎት 8 ኮምፒዩተር ጥገና…………………………… ብር 1200.00
ሎት 9 የተለያዩ እቃዎች ጥገና………………………. ብር 2400.00
ሎት 10 ቋሚ እቃዎች………………………………ብር 9080.00
ሎት 11 የወለል ምንጣፍ……………………………ብር 1800.00
ሎት 12 ሀይላንድ ውሀና ቆሎ……………………….. 1109.35
ተጫራቾች ከሚጫረቱበት እቃ ጋር ግንኙነት ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው በጨረታው ተካፋይ መሆን እንደሚችሉ የሚያመለከት ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ያቅራቢ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት ከሚጫረታቸው ሰነዶች ጋርአባሪ መሆን ይኖርበታል። የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 4 1ኛ ፎቅ ላይ መግዛት ይችላሉ.
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለት/ቤቱ ማስያዝ ይኖርበታል።
- የጨረታው ሰነድ ሲገባ ናሙና አብሮ መቅረብ አለበት። ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡበት ሰነድ ዋናውና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገት አለባቸው፡
- ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ከመስሪያ ቤታችን ጋር ውል ተዋውሎ የውል ማስከበሪያ ዋጋውን 10 % ዋጋ መስያዝ ይኖርበታል። በተጨማሪ የአሸናፈውን እቃ በ10ቀናት ውስጥ ማቅረብ ግዴታ አለበት። ይህ ባይሆን ግን ለጨረታው የተያዘውን ቼክ ዋጋ በቀጥታ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል።
- ጨረታው የመጨረሻ ቀን በማግስቱ 4፡00 ሰአት ይዘጋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰአት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገዱ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 ክልል ውስጥ የሚገኘው የእውቀት አምባ ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ / ደ/ ት / ቤት
