በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ እና አላቂ እቃዎች እንዲሁም የመኪና ዕቃ መለዋወጫ በግልፅ የጨረታ አግባብ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የሴ/ግ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ እና አላቂ እቃዎች እንዲሁም የመኪና ዕቃ መለዋወጫ በግልፅ የጨረታ አግባብ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ-
-
ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገበ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የግዥ መጠኑ ብር 200,000 እና ከዚህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት መረጃ ማቅረብ የሚችል
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ለጽህፈት መሳሪያና ለአላቂ እቃዎች 15,000 ብር፣ ሎት 2 ለመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች 10,000 ብር እና ከዚያ በላይ ማሲያዝ እንደሚጠበቅባቸው ይኸውም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፅ/ቤታችን ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብራችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
-
ተጫራቾች በጨረታ መከፈቻ ወቅት እንዲገኙ አይገደዱም ነገር ግን በጨረታው መገኘት አለብን ብለው ካሰቡ መገኘት ያለበት አካል የተጫረተው ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው አካል ኦርጅናል የውክልና ማስረጃውን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
-
ተጫራቾች ሁሉንም ዕቃ በየሎቱ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፍል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በኤ/ግ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
-
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ5/13/17ዓ.ም እስከ 14/1/18 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ማለትም በ 15/1/18 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
-
ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
-
ተጫራቾች ለወሰዱት የተጫራች መመሪያ /የጨረታ ሠነድ/ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ሙሉ በሙሉ መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
በየሎቱ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው አሸናፊ ስለሚሆን ለእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ሙሉ በሙሉ ጨረታው ላይ ዋጋ መሞላት አለበት ይህ ካልሆ ግን ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
-
አሸናፊ የሆነው ተጫራች እያንዳንዱን እቃ በሚፈለገው የጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል በሞዴል 19 ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ ገቢ ላደረገበት እቃ ሞዴል 19 በመያዝ ክፍያ ይፈፀምለታል፡፡
-
ጽ/ቤቱ ግዥውን በ20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
-
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ:- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፡፡
* ጨረታውን በተመለከተ በስልክ ቁጥር በ0336611359 ወይም 0913274951 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የሴ/ግ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት
