Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline24 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  • opening date2025-09-24 00:00:00
  • Categories Engineering Consultant

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሎት አንድ (Lot-1) የተማሪዎች ማደሪያ ማስፋፈያና ተያያዥ መገልገያዎች እንዲሁም ለሎት ሁለት (Lot-11) አዲስ ትምህርት ቤት ፕሮጀክት ግንባታ ማስተር ፕላንና ዲዛይን ክለሳ፡ የግንባታ ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር የምክር አገልግሎት የሚሰሩ ደረጃ አንድ የማማከር ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T572

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሎት አንድ (Lot-1) የተማሪዎች ማደሪያ ማስፋፈያና ተያያዥ መገልገያዎች እንዲሁም ለሎት ሁለት (Lot-11) አዲስ ትምህርት ቤት ፕሮጀክት ግንባታ ማስተር ፕላንና ዲዛይን ክለሳ፡ የግንባታ ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር የምክር አገልግሎት የሚሰሩ ደረጃ አንድ የማማከር ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። ፕሮጀክቱን የማጠናቀቂያ ጊዜ ስራው ከተጀመረበት በ 365 ቀናት ውስጥ ለሎት አንድ (Lot-1) እና በ 300 ቀናት ውስጥ ለሎች ሁለት (Lot-11) ይሆናል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፤

  1. ተጫራቹ 2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN) ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  2. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ከሚሰጥ ሕጋዊ አካል ለ2017 ዓ.ም የታደሰ ደረጃ አንድ ህንፃ ስራ ተቋራጭ የማማከር ፈቃድ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
  3. የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
  4. የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል!
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰላሳ (30) ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT- T572 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  6. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሁለት መቶ ሺህ ብር (200,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው (Conditional) የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል የጨረታ መክፈቻ ክፍል በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

አቶ አሊ አስፋው

ስልክ ቁጥር: 011-517-45-52

ኢ-ሜይል: AliAs@ethiopianairlines.com

 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

Save Tender