በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የአትልትና ፍራፍሬ ልማት መስኖ ውሃ አጠቃቀም ዳይሬከቶሬት በኢዩ ካፌ የበጀት ለስሜን ሜጫ እና ለባንጃ ወረዳ ለቡና ልማት ማስፈፃሚያ አገልግሎት የሚውል የቨርሚ ተስቦ ትል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የአትልትና ፍራፍሬ ልማት መስኖ ውሃ አጠቃቀም ዳይሬከቶሬት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የአትልትና ፍራፍሬ ልማት መስኖ ውሃ አጠቃቀም ዳይሬከቶሬት በኢዩ ካፌ የበጀት ለስሜን ሜጫ እና ለባንጃ ወረዳ ለቡና ልማት ማስፈፃሚያ አገልግሎት የሚውል የቨርሚ ተስቦ ትል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው ማለትም የቨርሚ ተስቦ Worm /ትል/ በማቅረብ የተሰማሩ እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና ግብር የከፈሉበትን ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
2.ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
3.የግዥው መጠን ብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ!
4.ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከአርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የሚገዙ የቨርሚ ወርም ትል ግዥ ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
6.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመከፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁርጥ 50,000.00 /ሀምሳ ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ በፖስታ ማቅረብ (ጥሬ ገንዘብ)በመ/ቤቱ በህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።ማንኛውም ተጫራች የጨረታ /የመወዳደሪያ/ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጂ ለየብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱ እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጂ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16ኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2205849/0583208095/በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡
12.በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ
