በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 8 ክልል የሚገኝ የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 1 ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጨረታ ቁጥር 02/2018 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል።
የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 1 ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የሁለተኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 8 ክልል የሚገኝ የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 1 ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጨረታ ቁጥር 02/2018 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 አላቂ የጽህፈትና የትምህርት እቃዎችና መገልገያዎች
ሎት 2. የፅዳት እቃዎችና መገልገያዎች
ሎት 3. የደንብ ልብስ
ሎት 4. ቋሚ እቃዎች ግዥ እና
ሎት 5. የህትመት ስራዎች
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሠርተፊኬት ያላቸው፣
2. የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
3. ለመጫረት የሚያበቃ ሙሉ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ የቀራንዮ መ/ዓለም ቁጥር 1 ቅድመ እንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሂሳብ ከፍል በመምጣት በየሎት ብር የማይመለስ 300.00(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ቅጅ/ኮፒ/ ለየብቻ የጨረታ ማስከበሪያ CPO/ሲፒኦ/ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቤቱ ላይብረሪ አዳራሽ ይከፈታል።
6. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች ከአደራጃቸው አካል ለጨረታ ሰነድ በነፃ እንዲወሰዱ ፤ በጨረታ ማስከበሪያ እና በውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በግልፅና በዝርዝር በተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር የምትችሉት ባመረታችሁት እቃ ብቻ ሲሆን አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ ከአደራጃችሁ ጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
8. ማንኛውም ተጫራች በመ/ቤቱ የተዘጋጀውን ዝርዝር ፍላጎቶች እና መደበኛ የጨረታ ሠነድ በመውሰድና የሚሞላውን ክፍል በሙሉ በመሙላት እና ሁሉም ገፆች ላይ ተፈርሞና ማህተም ተረጋግጦ ለመ/ቤቱ ተመላሽ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንገልፃለን።
9. የመ/ቤቱ የዕቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ /የቴክኒክ ኮሚቴ/ የሚያቀርቡትን የዕቃዎቹን ጥራት አይቶ መ/ቤቱ ጥራት የጎደለው ነው ብሎ ካመነ ዕቃው እንዲመለስ ማድረግ ይችላል።
10.የጨረታው አሸናፊ ድርጅት /ድርጅቶች/ ማሸነፉ እንደተገለፀለት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ተደርጎበት መ/ቤቱ 2ኛው የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋበዝ ይችላል።
11. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል የገንዘብ መጠን በየጨረታሎትተከፋፍሎ እንደሚከተለው የቀረበ ሲሆን ለምትወዳደሩባቸው የጨረታ ሎቶች በCPO ማቅረብ አለባችሁ።
|
የሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር |
|
1 |
አላቂ የጽህፈትና የትምህርት እቃዎችና መገልገያዎች |
20,600.00 |
|
2 |
የዕዳት እቃዎችና መገልገያዎች |
16,000.00 |
|
3 |
የደንብ ልብስ |
18,000.00 |
|
4 |
ቋሚ እቃዎች |
28,000.00 |
|
5 |
የህትመት ስራዎች |
1,000.00 |
12.በጨረታ ማስከበሪያነት የተያዘሉን ሲፒኦ በመውሰድ እና ተጫራቾች ውል እንዲዋዋሉ ከመ/ቤቱ ሲገለፅላቸው ያሸነፉበትን የዋጋ ድምር 10% በውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በመስሪያ ቤታችን ስም በርPO ማስያዝ ይኖርባችኋል።
13.የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተውን የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
14.ጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘረዘሩት ውጭ በጥራት የሚበልጥና የሚስተካከል ዋጋ ያለው ዕቃ በማቅረብ መወዳደር ይቻላል።
15.ጨረታ አሸናፊ የሆናችሁ ድርጅቶች ያሸነፋችሁበትን እቃ መ/ቤታችን ንብረት ከፍል ድረስ በማስገባት ማስረከብ ይኖርባችኋል።
16.ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡባቸው የተመረጡትን ዕቃዎችን በፍላጎት ዝርዝሩ ላይ ምርመራ በሚለው ሳጥን ስር የተገለፀ ሲሆን ናሙናው እስከ ግልፅ ጨረታ ማለቂያ ቀንና ሰዓት በፊት ማቅረብ አለባቸው።
17.አንድ ተጫራች ሌላው ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
18.ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በጦርኃይሎች በሆላንድ ኤምባሲ ቀራንዮ አደባባይ
ወደ ቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤተ ከርስቲያን መግቢያ በስተቀኝ በኩል 100 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር:- 011-8-67-86-59/011-8-27-74-51/011-8-27-74-52/
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 8 ክልል የቀራንዮ ቁጥር 1 ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
