በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር አፄ ናኦድ አንደኛና እና መካከለኛ ደረጃት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ግዥ የሚያስፈልገውን፡ የተለያዩ አላቂ የትምህርት፣ አላቂ የቢሮ፣ የፅዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ የስፖርት እቃዎች፣ አላቂ የህክምና እቃዎች ፣የህንፃና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ቋሚ እቃዎች እና የማባዥያ ማሽን ጥገና፣ልዩ ልዩ የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር አፄ ናኦድ አንደኛና እና መካከለኛደረጃት/ቤት
ግልጽ የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር አፄ ናኦድ አንደኛና እና መካከለኛ ደረጃት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ግዥ የሚያስፈልገውን፡ የተለያዩ አላቂ የትምህርት፣ አላቂ የቢሮ፣ የፅዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ የስፖርት እቃዎች፣ አላቂ የህክምና እቃዎች ፣የህንፃና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ቋሚ እቃዎች እና የማባዥያ ማሽን ጥገና፣ልዩ ልዩ የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ጨረታውን ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ በማሟላት የጨረታ ሰነዱን ከአጼ ናኦድ አንደኛና እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ዘወትር በስራ ሰዓት እየመጡ መውሰድ ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. በመንግስት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል Tin No. ያላቸውና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የጨረታውን ሰነድ በነፃ ይጦስዳሉ ከአደራጃቸው ተቋም ወቅታዊ የሆነ _ በአድራሻችን የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያና ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ብር5000.00(አምስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በአራዳ ከ/ከተማ አስተዳደር የአፄ ናኦድ አንደኛና እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደርጠቅላላ አገልግሎት ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ _ አሸገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
8. ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት 11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዘኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአፄ ናኦድ አንደኛና እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡
9. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ ተሞልቶ ኦርጅናሉና ኮፒው ተለይቶ በፖስታው ላይ ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል። ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም።
10. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ያልቀረበበት እና የዘገየ በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ እንዲሁም ከጨረታ ሠነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
11. ተጫራቾች 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
12. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚቀርብበት ምርት/ዕቃ ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ምርት/ዕቃ ከገበያ ላይገዝተው ለሚወዳደሩት እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ለግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡ መ/ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-ከአራት ኪሎ ወደ ቅድስት ማሪያም ፊት ለፊት የቀድሞው ሸዋ ዳቦን ፊት - ለፊት
ስልክ ቁጥር፡-0111542338 /0111245187
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የአፄ ናኦድ ስንደኛናእና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
መንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን
