የሸዋሮቢት ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በግቢው ውስጥ ያለውን DCI PIPE በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እገልፃለን።
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሸዋሮቢት ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በግቢው ውስጥ ያለውን DCI PIPE በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እገልፃለን።
1. በዘመኑ የታደሠ ሀጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸው
3. የቫት ተመዝጋቢ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሡትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሸ/ከ/አስ/ውኃ አገልግሎት ድርጅት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ ሠነዱን በማይመለስ ብር 1000.00 ( አንድ ሺ ብር ) ከድርጅቱ ዘወትር በስራ ሠዓት ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ)ማስያዝ አለባቸው::
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸ/ከ//ውኃ አ/ሎት ድርጅት ማስታወቂያው በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 3፡00 ሠዓት ይከፈታል። የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል።
9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
10. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ያሸነፉትን ማንኛውንም ንብረት በራሱ ትራንስፖርት ወጭማጓጓዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታውን ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ድርጅታችን ድረስ በአካል በመገኘት (በስልከ ቁጥር 0336640040 /0913519898) በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሸዋሮቢት ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
