Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት ቅጥር ግቢ ውስጥ በስተምስራቅ ወይም ጎሮ በኩልና 1 በጀነራል አቪዬሽን ኤፕረን ዙሪያ፣ የነዳጅ ዴፖ እና ፈደራል ፖሊስ መኖሪያ ህንጻ አካባቢ የመሬት ማስዋብና አረንጓዴ ማልበስ ስራ ፣ በቡልቡላ በኩል የመዳረሻ መንገድ ግንባታና የቆሻሻ ወይም ተረፈ ምርት ቦታ ማስተካከል ዲዛይን እና ግንባታ ስራ ፕሮጀክት (Design and Build of Landscape and Greenery Works at East (Goro) Side and Around General Aviation Apron, Fuel Farm and Police Residence, Access Road Construction and Preparation of Garbage Area at Bulbula Side of Addis Ababa Bole International Airport) ለማሰራት ስራ ተቋራጭ ተወዳዳሪዎችን በጨረታ ለመጋበዝ ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ቁጥር፡ -SSNT-T566

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት ቅጥር ግቢ ውስጥ በስተምስራቅ ወይም ጎሮ በኩልና 1 በጀነራል አቪዬሽን ኤፕረን ዙሪያ፣ የነዳጅ ዴፖ እና ፈደራል ፖሊስ መኖሪያ ህንጻ አካባቢ የመሬት ማስዋብና አረንጓዴ ማልበስ ስራ ፣ በቡልቡላ በኩል የመዳረሻ መንገድ ግንባታና የቆሻሻ ወይም ተረፈ ምርት ቦታ ማስተካከል ዲዛይን እና ግንባታ ስራ ፕሮጀክት (Design and Build of Landscape and Greenery Works at East (Goro) Side and Around General Aviation Apron, Fuel Farm and Police Residence, Access Road Construction and Preparation of Garbage Area at Bulbula Side of Addis Ababa Bole International Airport) ለማሰራት ስራ ተቋራጭ ተወዳዳሪዎችን በጨረታ ለመጋበዝ ይፈልጋል።

የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በ180 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ ይሆናል፣

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች፣ አስፈላጊውን የሰው ሃይል፣ ማሽንና የግንባታ ግብዓት ማሟላት የሚችሉ ሥራ ተቋራጮች ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ ለማሰራት ለ2017 ዓ.ም በንግድ ሚኒስቴር የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤
  2. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል የታደሰ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GC-1/RC-1) የሆነ፤ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤
  3. ጨረታው ግልጽ ጨረታ ሲሆን በዶክመንቱ ላይ በተገለጸው መሰረት ለሁሉም የአገር ውስጥና የውጭ አለም አቀፍ ተጫራቾች ክፍት ነው።

የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣

የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡

የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር

የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሶሰት መቶ ብር (300.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T566 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ እና ቅድመ-ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን ታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517- 89-53

ልመንህ ጋሻው

ኢ-ሜይል: LimenihG@ethiopianairlines.com

 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

Save Tender