የትምህርት ብልጭታ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚሰሩ በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ማህበራት የተደራጁ ህጋዊ የሥራ ተቋራጮችን ሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
የትምህርት ብልጭታ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ስራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚሰሩ በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ማህበራት የተደራጁ ህጋዊ የሥራ ተቋራጮችን ሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል።
ተቋራጮች ማሟላት ያስባቸው መስፈርቶች
|
ተ.ቁ |
የስራው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
ደረጃ |
የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን |
የጨረታ ማስገቢያ ቀን |
የጨረታ መክፈቻ |
|
|
የትምህርት ብልጭታ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የህንፃ አድሳትና ፖርቲሽን ስራ |
ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ |
በጥቃቅንና አነስተኛ ታዳጊ እና መብቃት |
በጋዜጣው ከወጣበትቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2፡30-10:30 ሰዓት |
በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ |
በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከ4፡15 ጀምሮ |
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
2. በዘርፉ የ2017/2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ከሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡና ምስከር ወረቀት ያላቸው፤
4. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌዴራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራከሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ የትምህርት ብልጭታ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ስራ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ቀርበው ሠነዱን 200 ብር/ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ጨረታው የሚከፈተው በ22ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 የሚከፈት ይሆናል።
7. የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴከኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. አሰሪው መ/ቤት _ አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ (Instruction to Bidder (ITB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይገደዳሉ፡፡
10.ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ፤ ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብይኖርባቸዋል።በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል። በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
11. ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኢንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን የትምህርት ብልጭታ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ስራ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
12.ተጫራቾች ከዚህ በፊት ት/ቤቱ ባስገነባቸው ግንባታዎችም ሆነ እድሳቶች ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
13.አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል።
14.ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15.ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ22ኛው ተከታታይ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ የትምህርት ብልጭታ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር03 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
16.ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደጃጅ ውቤ በሚገኘው የትምህርት ብልጭታ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እድሳት ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በግንባር በመቅረብ ወይም
ስልክ ቁጥር- 011 1 26 62 73 /011 1 56 57 06 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የትምህርት ብልጭታ የጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
