በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውብት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
በጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና
የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 11/2018
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውብት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሐሙስ ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡
በመሆኑም፤
1. በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼከ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን፤ ለሐራጅ ጨረታ ደግሞ ከጨረታ አንድ ቀን በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡
2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሐሙስ ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼከ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMIS-SION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼከ (CPO) በተ.ቁ 4 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡ ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ቼከ (CPQ) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
6. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
የእቃ ሐራጅ |
እስከ 03/13/2017 |
04/13/2017 4:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
|
የእቃ ግልጽ |
እስከ 04/13/2017 |
05/13/2017 3:45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል። |
7. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፦ አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
8. ተሽናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
11. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩከ ፡- 011-470-85-03
አድራሻ፦ ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
