በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ማለትም ሎት 1 የጽህፈት ዕቃዎች፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 ልዩልዩ ዕቃዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 ቋሚ ዕቃዎች፣ ሎት 6 ኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ሎት 7 የህከምና ዕቃዎች፣ ሎት 8 ኤሌከትሮኒከስ ጥገና፣ ሎት 9 የትምህርት ዕቃዎች እና ሎት 10 የግንባታ ጥገናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ማለትም ሎት 1 የጽህፈት ዕቃዎች፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 ልዩልዩ ዕቃዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 ቋሚ ዕቃዎች፣ ሎት 6 ኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ሎት 7 የህከምና ዕቃዎች፣ ሎት 8 ኤሌከትሮኒከስ ጥገና፣ ሎት 9 የትምህርት ዕቃዎች እና ሎት 10 የግንባታ ጥገናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
1. በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
የሎት ቁጥር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር |
|
ሎት 1 የጽህፈት ዕቃዎች |
ብር 17900 |
|
ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች |
ብር 16800 |
|
ሎት 3 የልዩ ልዩ ዕቃዎች |
ብር 10600 |
|
ሎት 4 የደንብ ልብስ |
ብር 18500 |
|
ሎት 5 ቋሚ ዕቃዎች |
ብር 18000 |
|
ሎት 6 የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች |
ብር 13400 |
|
ሎት 7 የህከምና ዕቃዎች |
ብር 1000 |
|
ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና |
ብር 7400 |
|
ሎት 9 የትምህርት ዕቃዎች |
ብር 4600 |
|
ሎት 10 የግንባታ ጥገናዎችን |
ብር 18000 |
6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር100 (አንድ መቶ) በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 05 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
8. ጨረታው በአስረኛው ቀን በ10፡ዐዐ ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዚጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
10 ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
12. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ስልክ፡- 0118681536 / 0118681537
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ መሪ ገበያ 500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት
