Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚንስቴር ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Ministry of Revenues (የገቢዎች ሚኒስቴር)


 

በታክስ ዕዳ የተያዙ የመኖሪያ ቤት፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች የተለያዩ ንብረቶችን ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ 01/2017

 

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚንስቴር ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ለገዳዲ ለገጣፎ ከተማ ላይ ያለ 500ካ.ሜ ላይ ያረፈ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰራ መኖሪያ ቤት፤ ከሜጋ ቪሌጅ ሪልእስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የኮንስትራክሽን እቃዎች (እስካፎልዲንግ)፣ ከፎኔክስ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (የፕላስቲክ ገመድ መጠቅለያ ማሽን)፣ ከኡኑፕሬሳ ኮንስትራክሽን እና ከሰንራይዝ ስቲልነስ ፕሮዳክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ኮምፒውተር ፕሪንተር እና የመቁረጫ ማሽኖች) ፤ከፒጂኤ ቴክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከሜትሮ ኮሚኒኬሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከሲቲ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ፤ ከፓትሮል የጥበቃ አገልግሎት፣ ከጄቢ ኮንስትራከሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ከአቶ ተክኤ ዘርአይ ገ/መድህን የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን 6 ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም

  1. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታውቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ህንፃ “ለ” 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ "ሀ" 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ /10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚንስቴር ስም (Minstry of Revenue) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በሚከተሉት የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የመስሪያ ቤቱ ስም

ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት

የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ገቢዎች ሚኒስቴር

ለገጣፎ ከተማ በካርታ ቁጥር OR042012004005 ተመዝግቦ የሚገኝ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰራ መኖሪያ ቤት፤ ኮምፒውተር፤ ፕሪንተር፤ የመቁረጫ ማሽኖች፤ የፕላስቲክ ገመድ መጠቅለያ ማሽን፤ እስካፎልዲንግ እና የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች

ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት እና ለ30 ቀናት

የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች እስካ ፎልዲንግ፣ የፕላስቲክ ገመድ መጠቅለያ ማሸን፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር እና የመቁረጫ ማሽኖች ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን የመኖሪያ ቤቱ ጋዜጣው በወጣ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ በ31ኛው ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

  1. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- መገናኛ በሚገኘው በሚንስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት/ ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
  2. የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
  3. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  4. የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፋበትን ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚንስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  7. ሚንስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-617-84-90 ኮድ (2044) (2045) (2046) የውስጥ መስመር (EXT) 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MOR.Gov.et መመልከት ይቻላል፡፡

 

የገቢዎች ሚኒስቴር

 

Save Tender