Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ህክምናና ላብራቶሪ ግቢ ውስጥ አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 226 3095
  • Websitehttps://amharaforest.gov.et
  • Deadline10 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-09-10 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል፡፡

Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)


                                      በድጋሚ የወጣ የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት የጨረታ ሰነድ ቁጥር አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ                   

                                                         የጨረታ ሰነድ ቁጥር አደ-ግ /ጨ-005/2018 

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል፡፡ 

  1. የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር Tax Identification Number (TIN) ያለው

  2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ፡ 

  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪ አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ካደረጓቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ 

  4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ። 

  5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር ከፍሎ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይቻላል።

  6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመመላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ” የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bod/ ማሲያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 13 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል:: 

  7.  7. የጨረታ ሳጥኑ በıoኛው ቀን ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ከሆነ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ወይም እለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ከቀኑ 8፡30 ወይም የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ ከሆነ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ 

  8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡: 

                ማሳሰቢያ፡ ተጨማሪ _ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0583202985/0986813855 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል 

                አድራሻ፡-ባህር ዳር ከተማ

                                                                                   የአማራ ደን  ኢንተርፕራይዝ

Save Tender