በደቡብ ምዕ/ኢ.ት/ሕ/ ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በዲንቢራ ከተማ ቅድመ መደበኛ ት/ቤት ለተማሪዎች የመማሪያ ክፍል ግንባታ ሥራ ለማሠራት በዘርፉ ብቁ የሚሆኑ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2018
በደቡብ ምዕ/ኢ.ት/ሕ/ ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በዲንቢራ ከተማ ቅድመ መደበኛ ት/ቤት ለተማሪዎች የመማሪያ ክፍል ግንባታ ሥራ ለማሠራት በዘርፉ ብቁ የሚሆኑ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል
- ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣
- ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ቲን ነምበር ያለውና የቫት ተመዝጋቢነቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነድ አንድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለእያንዳንዳዱ ሁለት ሁለት ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው የሚሣተፉ ድርጅቶች በወረዳው ውስጥ ባሉ ፕሮጀክቶች ላይ አሸናፊ በመሆን የሚሠሩ ከሆነ የሥራውን አፈጻጸም 75 በመቶ እና ከዚያ በላይ ስለመፈጸሙ ከአሠሪው መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች መልካም የሥራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ቢያቀርቡ ይመረጣል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO /ማስያዝ የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ ብቻ እየከፈሉ ከሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 5 ዘወትር በስራ ሰአት ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ22ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ተጫራቾች/ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚታሸግ ሲሆን በታሸገበት ዕለት ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ የተጫራቾች/ህጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሰነድ የመክፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
ማሳሰቢያ- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0476680200/0431 በመደወል መረዳት ይቻላል ::
በደቡብ ምዕ/ኢት/ሕ/ ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
